ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በልማት እቅዶችና ፍላጎቶች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከሶማሊላንድ ፕላንና ልማት ሚኒስትር አሕመድ ሞሃመድ ድሪር (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ሁለቱ ሚኒስትሮች በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በተለይም በመሪ የልማት እቅዶች እንዲሁም የልማትና የእድገት ፍላጎቶች መሰረት ባደረጉ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!