“የአእላፋት ዝማሬ” የተሰኘ የምስጋና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን አስመልክቶ “የአእላፋት ዝማሬ” የተሰኘ መርሐ ግብር በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኒዓለም ካቴድራል እየተካሄደ ነው፡፡
መርሐ ግብሩን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስጀምረውታል፡፡
የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር ባዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናንና ምዕመናት ተሳትፈዋል፡፡
የመዝሙር ጥናቱን ተሳታፊዎች ከሦስት ወራት በፊት ጀምረው ልምምድ ሲያካሄዱ መቆየታቸውን አዘጋጆች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በምንይችል አዘዘው