የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በአርመን፣ ሩሲያ፣ ግብጽ፣ ቤላሩስ፣ ጆርጅያ፣ ካዛኪስታን፣ ሞልዶቫ፣ ሞንቴነግሮ ሰርቢያና በሰሜን መቄዶንያ በተለያየ ሐይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስትያን÷ በፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መሪነት በመንበረ- ፓትርያርክ ቅድስተ-ቅዱሳን ማርያም ገዳም በዓሉን አስመልክቶ ሥርዓተ-ቅዳሴ ተካሂዷል፡፡
እንዲሁም የኢየሱስ ክርቶስ የልደት ዕለት ከቅዱስ ላሊበላ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ተከትሎ በቅዱስ ላሊበላ ገዳም በቤዛ ኩሉ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ተከብሯል፡፡
በሌላ በኩል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እንዲሁም የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ክሪል እና የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተገኙበት መከበሩ ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ በመሩት ሥርዓተ- ቅዳሴ እንዲሁም በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በዓሉ በሥርዓተ-ቅዳሴ መከበሩን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
በክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ÷ የይቅርታ፣ የዕርቅ እና ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሸጋገር ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የልደት በዓል በየዓመቱ ታኅሣስ 29 እንደሚውል የሚታወቅ ሲሆን÷ ልክ እንደዘንድሮው በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ዮሐንስ በታኅሣስ 28 ይውላል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!