Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን በማስመልከት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ አጋሩ።

የገና በዓልን በማስመልከት በከተማዋ በሚገኙ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት የማዕድ ማጋራት ተከናውኗል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤም በቄራ የተስፋ ብርሃን ማዕከል በመገኘት ማዕድ ማጋራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቄራ የሚገኘው የተስፋ ብርሃን ማዕከል በቀን ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችን እየመገበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በመዲናዋ የተገነቡት 20 የምገባ ማዕከላትም በቀን ከ35 ሺህ ለሚልቁ ወገኖች የምገባ አገልግሎት እየሠጡ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

ማዕከላቱ አቅመ ደካሞችን፣ እናቶችንና አረጋውያንን ከመመገብ ባሻገር÷ ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.