Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎችና አምባሳደሮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና አምባሳደሮች የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት ለኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
በኢትዮጵያ የጀርመንና የጣልያን ኤምባሲዎች በመልካም ምኞት መልዕክታቸው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
 
በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ትብብር እንዳላቸው አመልክተዋል።
 
ለዘመናት በወዳጅነት፣ በመተማመን እና በመረዳዳት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚያጠናክሩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተናግረው የገና በዓልም ሰዎች ደስታን ያገኙበት በመሆኑ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
 
በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው “በኢትዮጵያ ገናን ለሚያከብሩ ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በተመሳሳይ የእስራኤል፣ የህንድ፣ የስዊዲን፣ የአውስትራሊያ፣ የእንግሊዝ እና የኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች “ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ” ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.