የሞተር ሳይክሎች እና ከባድ ተሸከርካሪዎች ክልከላ የተደረጉባቸው መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞተር ሳይክሎችና ከሁለት ቶን በላይ የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ የመይችሉባቸውን መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደርጓል ።
መንግዶቹ ቦሌ – በኦሎምፒያ – መስቀል አደባባይ – ብሔራዊ ቤተ -መንግሥት እንዲሁም አራት ኪሎ በሁለቱም አቅጣጫ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በመሆኑም የሞተር ሳይክል እና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ከታህሳስ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።
በመንግዶቹ ክልከላውን የሚገልፁ ምልክቶች መተከላቸውን ያስታወቀው ፖሊስ የተላለፈውን መልዕክት በማያከብሩ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡