አፈርን በኮምፖስት የማበልፀግ ልምምዳችንን በተሻለ ሁኔታ ካዳበርን ሰፊ ጥቅም እናገኝበታለን – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፈርን በኮምፖስት የማበልፀግ ልምምዳችንን በተሻለ ሁኔታ ካዳበርን ሰፊ ጥቅም ልናገኝበት እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስት ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷አፈርን በኮምፖስት ማበልፀግ በተለይም በከተማ ግብርና ሥራችን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርገናል ብለዋል።
ኮምፖስት የአፈርን ይዘት ያሻሽላል፤ ለጠንካራ የእፅዋት ስርዓት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤ የእፅዋት እድገት እና የጤንነት ደረጃን ይጨምራል ሲሉም ገልጸዋል፡፡