ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረው መሃመድ ሽኩር አበባውን ያየ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረው መሃመድ ሽኩር አበባውን ያየ ማንኛውም ግለሰብ ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ፡፡
በአስኮ አዲስ ሰፈር የጁሙዓ ኸጢብና የኪታብ አቅሪ የነበሩት ሸይኽ አብዱ ያሲን ከዒሻን ሰላት ሲመለሱ በተተኮሰቧቸው ጥይት ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡
ግድያውን ተክትሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።
በተደረገው ክትትልም የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ነዋሪ የሆነው እና ሟቹ ሼክ ያሲን ያሳድጉት መሃመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ እንደሚፈለግ ፖሊስ ገልጿል።
ስለሆነም ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረውን መሃመድ ሽኩር አበባውን ያየ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል፡፡