Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጋር በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ ጋር በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ ተወያዩ።

በሶማሊላንድ  ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጄኔራል መኮንኖች አቀባበል ተደርጎለታል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊል ድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማድረጋቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.