በአዲስ አበባ 210 ሺህ 586 አጠቃላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 210 ሺህ 586 አጠቃላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የተከናወነው በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደቡ ባለፈ የአገልግሎት መስጫ ዓይነቶች መሆኑን ነው የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መላክ መኮንን የገለጹት፡፡
የተሰጡት የወሳኝ ኩነት ምዝባ አገልግሎቶችም÷ 181 ሺህ 983 የልደት፣ 16 ሺህ 933 ጋየብቻ፣ 2 ሺህ 813 የፍቺ፣ 8 ሺህ 762 የሞት እንዲሁም 95 ደግሞ የጉዲፈቻ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
የግማሽ ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም÷ ልደት 96 ነጥብ 71 በመቶ፣ ጋብቻ 19 ነጥብ 76 በመቶ፣ ፍቺ 109 ነጥብ 61 በመቶ፣ ሞት 40 ነጥብ 76 በመቶ እና ጉዲፈቻ 55 ነጥብ 74 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል 76 ሺህ 229 ያላገባ ማስረጃ አገልግሎት እንዲሁም 67 ሺህ 410 የነዋሪነት አገልግሎት መስጠት መቻሉንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡
በጤና ተቋም ላይ እየተደረገ ያለውን ወቅታዊ ምዝገባ ከ33 የጤና ተቋማት ወደ 73 ማሳደግ መቻሉ እና በሸሪዓ ፍርድ ቤት ምዝገባ መጀመሩ ለተገኘው ስኬት አስተዋጽኦ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
በአንጻሩ የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋንን ማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች በሚፈለገው ልክ ትኩረት አለመሰጠቱ እንደ ክፍተት ይታያልም ነው ያሉት፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!