Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈረመው ስምምነት የወጣቶች ጥያቄና ድል ነው – ፌደሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ወጣቶች ዘንድ ለረጅም ጊዜ ሲነሳ የቆየው የወደብ ጥያቄ በስምምነት መመለሱ የትውልዶች ድል ነው ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን ገለጸ።

ፌደሬሽኑ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን ሁሉን አቀፍ የትብብር አጋርነት የመግባቢያ ሰነድ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ፥ ስምምነቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መስኮች ሰፋ ያለ የትብብር ማዕቀፍ ያካተተ ነው ብሏል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ጭንቀትና ቁዘማ ለማከም የሚያስችል አጋጣሚን እንደፈጠረ በመግለጫው ተነስቷል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች የረጀም ጊዜ ጥያቄ የሆነውን የወደብ ጥያቄ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ማሳካት መቻሉ ለአፍሪካ ቀንድ ልማትና ብልጽግና ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም ተመላክቷል ።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.