Fana: At a Speed of Life!

ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ከታህሳስ 18 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል  ነው 404 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 398 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፎች የያዘው፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሐኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የገቢ እና የወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ አዋሽ እና ድሬደዋ ጉምሩክ ቅርንጫፎች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽኑ በሕግ ማስከበር ሥራው የተሳተፉ ሰራተኞች፣ የክልሎችና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እንዲሁም ሕብረተሰቡን አመስግኗል፡፡

ድርጊቱን ለመከላከል ኮሚሽኑ ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ባላድርሻ አካላትና ሕብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.