በአማራ ክልል የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራዎችን በማስመልከት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሣህሉ (ዶ/ር) እንዳሉት ፥ በዘንድሮው ዓመት የተፋሰስ ልማትን በተጠናከረ መልኩ ለመስራት ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
ከነገው ዕለት ጀምሮም ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ነው የገለጹት፡፡
በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወነ ሥራ 15 ነጥብ 7 በመቶ የደን ሽፋን ላይ መደረሱ ተመላክቷል፡፡
በ2015 ዓ.ም የነበረው የተፋሰስ ሥራን መነሻ በማድረግ ዘንድሮ 9 ሺህ 60 ተፋሰሶችን ለማልማት ለአርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጥቶ የማልሚያ መሳሪያዎች ተለይተዋል ተብሏል።
በዚህም በ376 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደሚከን ተገልጿል፡፡
በስንታየሁ አራጌ