በኦሮሚያ ክልል 150 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር መደበኛ ኮምፖስት ለማዘጋጀት ታቅዶ እየተሰራ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል 150 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር መደበኛ ኮምፖስት ለማዘጋጀት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ፡፡
አቶ ሽመልስ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ በክልሉ ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዚህ መሰረትም በሁሉም ወረዳዎች ሞዴል የኮምፖስት ማቀነባበሪያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት፡፡
በተለይ ለትል ኮምፖስት ልዩ ትኩረት በመስጠት በ265 ወረዳዎች የዝግጅት ማዕከላት በ938 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በመገንባት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ማዕከላቱ በሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ እንደሚገነቡ ነው የጠቆሙት።
በተያዘው ዓመትም 150 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር መደበኛ ኮምፖስት ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን 119 ነጥብ 77 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የትል ኮምፖስት ለማዘጋጀት ታቅዶ ፥ እስካሁን 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ማዘጋጀት መቻሉን አንስተዋል፡፡
አሁን ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት የሚሆኑ ግብዓቶች በብዛት የሚገኙበት ወቅት በመሆኑ አርሶ አደሮች አጋጣሚውን በመጠቀም የአፈርን ጤናና ለምነት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዚህም አመራሩና ባለሙያዎች የድርሻቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አሳስበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!