የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የአፈር አሲዳማነትን ለመከላከል 276 ሚሊየን ብር ተመድቧል ተባለ

By Alemayehu Geremew

January 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የአፈር አሲዳማነትን ችግር ለመከላከል 276 ሚሊየን ብር መመደቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ከድር÷ በክልሉ 43 ከመቶው መሬት አሲዳማ በመሆኑ ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአፈር አሲዳማነትን ለማከም ያስችል ዘንድ በክልሉ ያለውን የኖራ ፋብሪካ የማምረት ዐቅም የማሳደግ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

በተደረገው ጥረትም የኖራ ፋብሪካው ዓመታዊ የማምረት አቅሙ እንዲያድግ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

በክልሉ በአሲዳማነት የተጠቃውን መሬት ለማከም በአጠቃላይ ከ63 ሚሊየን ኩንታል በላይ ኖራ እንደሚያስፈልግ የተመላከተ ሲሆን ለዚህም 276 ሚሊየን ብር ተመድቦ ወደ እንቅስቃሴ መገባቱ ነው የተጠቆመው፡፡

ፍላጎቱን በፍጥነት ለሟሟላት የሲሚንቶ እና የጂፕሰም ፋብሪካዎች ጭምር ኖራ እንዲያመርቱ እየተደረገ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በአልማዝ መኮንን