በኦሮሚያ ክልል ከ455 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድ ግንባታ ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ ከ455 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 227 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን አዳዳስ የመገድ ግንባታ መከናወኑን የቢሮው ምክትል እና የመንገድ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ከድር ሁሴን ተናግረዋል፡፡
ይህንን ለማከናወንም 455 ሚሊየን 187 ሺህ 638 ብር ወጪ መደረጉን ገልጸዋል።
በ2016 የበጀት ዓመት 1 ሺህ 644 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ለማከናወን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በአጠቃላይ በግንባታ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ የታቀደውን ሥራ ለማከናወንም 3 ቢሊየን 296 ሚሊየን 932 ሺህ 926 ብር መመደቡን ጠቅሰዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!