Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፏን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር በጋራ እየሰራሁ ነው አለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደርን ሚሮስላቭ ኮሴክ ጋር ባደረጉት ውይይት፥ የኢትዮጵያን የማዕድን ሃብት ለዘላቂ ልማት ለማዋልና የስነ-ምድር አሰሳና ፍለጋ ጥናት ለማሳደግ በጋራ እንደሚሰሩ መክረዋል።

የማዕድን ዘርፉን በቴክኖሎጅ ለማዘመን እና የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር በጋራ እንደሚሰሩም ማረጋገጣቸውም ተነግሯል፡፡

አምባሳደር ሚሮስላቭ ኮሴክ እንደገለጹት፥ ሀገራቸው ከሚኒስቴሩ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመስራትና ተሞክሮዋን ለማካፍል ዝግጁ ናት፡፡

የቼክ ሪፐብሊክ ባለሙዎች ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ጋር በማዕድን አሰሳና የፍለጋ ምርምር በጋራ እየሰሩ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ዘርፉን የበለጠ በቴክኖሎጂ፣ በአቅም ግንባታና በስልጠና ለመደገፍ በትብብር እንደሚሰሩም ነው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.