ቴክ

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ የሞባይል መተግበሪያዎች ተዘጋጁ

By Tibebu Kebede

May 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሁለት የኮሮናቫይረስ ወረርሽ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ የሞባይል መተግበሪያዎችን አዘጋጀ።

ከመተግበሪያዎቹ መካከል አንደኛው በኮረናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ያለውን ንክኪ የሚለይ ነው።

ይህ መተግበሪያ በብሉቱዝ ብቻ ግንኙነት የሚያደርግና በሁለት ሜትር ርቀት ላይ መረጃውን የሚያሳይ መሆኑም ነው ዛሬ ኢንስቲትዩቱ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሲሰጥ ያመለከተው።

ሌላኛው መተግበሪያ ደግሞ በኮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የሚከታተሉ የጤና ባለሙያዎች ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያግዝ ነው።

መተግበሪያዎቹን ከኢንስትቲዩቱ ድረገጽ እና ከጎግል ፕሌይ ላይ ደቦ እና ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ በሚል አውርዶ መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል።

ኃይለ ኢየሱስ ስዩም