አቶ ደስታ ሌዳሞ በኢንቨስትመንት ለባለሐብቶች የተሠጡ መሬቶች ያሉበትን ሁኔታ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሐዋሳ ከተማ እንዲለሙ ለባለሐብቶች የተሰጡ የኢንቨስትመንት መሬቶች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅትም የኢንቨስትመንት መሬት ለታለመለት ዓላማ ሊውል እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል፡፡
ሥራዎችም በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ባለሐብቶች በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ማስታወቃቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የክልሉ መንግሥትም ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡