ቢዝነስ

የንግድ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለ10 ቀናት ተራዘመ

By Mikias Ayele

January 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለቀጣዮቹ አሥር ቀናት መራዘሙን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሲስተም መቆራረጥ እና ከክልሎች አወቃቀር ጋር በተያያዘ የንግድ ፈቃድ እድሳት ሂደቱ በመስተጓጎሉ ለሚቀጥሉት አሥር ቀናት ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

አጋጣሚው ነጋዴዎች የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎትን ያለ ቅጣት ማግኘት የሚችሉበት መሆኑም ተገልጿል፡፡