Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ ከተመድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና እንቅስቃሴ፣ በወቅታዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውኅደት እንዲፈጠር በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗንም አምባሳደር ምስጋኑ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን እና ከሌሎች የጎረቤት ሀገራት ጋር በመሠረተ-ልማት ትስስር እና በሌሎች ዘርፎች ላይ እየሠራች እንደምትገኝም አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውኅደት መጠናከር ለዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ቁልፍ መፍትሔ አድርጋ እንደምትመለከተውም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ከሆኑት በርክ በራን ጋር በወቅታዊ፣ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.