Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል የተማሪዎች ምዘና ፈተና መስጠት ጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የ2016 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች አጋዥ የትምርት ድጋፍ ለመስጠት የተዘጋጀ የተማሪዎች ምዘና ፈተና ዛሬ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ጀምሯል።

የምዘና ፈተናው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አጋዥ የትምርት ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነዉ ተብሏል።

በዚህም በክልሉ ሁሉም ዞኖች በአጠቃላይ 21 ሺህ ተማሪዎች የምዘና ፈተናዉን እንደሚወስዱ መገለፁን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱላሂ አብዲ÷ የምዘና ፈተናዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ የመጣውን የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል እና የትምህርት ጥራትን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.