Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የጤናማ እናትነት ወር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የጤናማ እናትነት ወር ዛሬ መጀመሩን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት÷ ወሩ የሚከበረው “ፍትሐዊነት፣ ተደራሽነት እና ጥራት ያለውን የቅድመ ወሊድ ክትትል በወቅቱ በማስጀመር ጤናማ እናትነትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

የጤናማ እናትነት በ2030 ለማሳካት ከተያዙት የልማት ግቦች አንዱ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የዘንድሮው የጤማ እናትነት ወር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ተጎጂ የሆኑ እናቶችን በማሰብ፣ በአከባቢያቸው የጤና አገልግሎትን መልሶ ማቋቋምን ትኩረት አድርጎ ይከበራል ብለዋል፡፡

የጤናማ እናትነት ወር በወርሃ ጥር ብቻ ተከብሮ የሚያበቃ ተግባር አለመሆኑን ያስታወቁት ሚኒስትሯ÷ ዓመቱን ሙሉ የሚሰራበት መሆኑን በመገንዘብ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.