Fana: At a Speed of Life!

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ምርት ‘‘ነሀቢ’’ የተሰኘ መተግበሪያ በይፋ ስራ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸዋ ቴክኖሎጂ ምርት ‘‘ነሀቢ’’ የተሰኘ መተግበሪያውን ዛሬ በይፋ ስራ አስጀምሯል።

በ2030 ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተቋም ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ የሚገልጸው አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ፤ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለህዝብ አቅርቧል፡፡

የዌብ ሳይት እና ተያያዥ ቁልፍ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ የታመነበት “ነሀቢ” የተሰኘ መተግበሪያንም በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል።

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳንኤል በቀለ እንደተናገሩት፥ ነሀቢ መተግበሪያ ከመቶ በላይ የመስሪያ አማራጮችን የያዘ ደህንነቱ የተጠበቀ ጊዜን ቆጣቢ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ ነው።

ነሀቢ መተግበሪያን በመጠቀም ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ድርጅት የራሳቸውን የቢዝነስ ዌብ ሳይት በመክፈት ስራቸውን ማስተዋወቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደሆነ ተገልጿል።

በማህሌት ተ/ብርሃን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.