ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ዝግጅቶች መሰናዳታቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ለሚኖሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው ለሚመጡ ወገኖች አምስት ዋና ዋና ዝግጅቶች መሰናዳታቸው ተገለፀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በተለያዩ ሀገሮች የሚኖሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር እየገቡ መሆኑን የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ገልጿል፡፡
በመግለጫውም 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሚካፈሉበት አምስት የተለያዩ ዝግጅቶች መሰናዳታቸው ተገልጿል::
ሁነቶቹም የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያንን ልዩ ባህሪና ወቅቶችን ጨምሮ ሌሎችንም መሰረት ያደረጉ ናቸው ተብሏል፡፡
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሳምንት ሲሆን÷ በዚህም የሀገራቸውን ወግና ባህል እንዲያውቁ የሚያስችል ነው ተብሏል።
በዚህ ሳምንት ከሚከወኑት መካከል የኢትዮጵያ ጣዕም አንዱ መሆኑን እና በዚህም የብሄር ብሄረሰቦች የተዘጋጁ ምግቦች ይቀርባሉ ነው የተባለው።
ሁለተኛው የእደ ጥበብ ውጤቶችና ምርቶች የሚቀርቡበት ነው በዚህም የእጅ እና የእደ ጥበብ ምርቶች የሚቀርቡበት ነው ተብሏል።
ሶስተኛው የኢትዮጵያ ድምፆች እና ውዝዋዜዎች ሲሆን÷ የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች ለህዝብ እይታ የሚቀርቡበት እና የሙዚቃ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።
አራተኛው የባህል አልባሳት የሚቀርቡበት ሲሆን፤ በዚህም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት እንደሚቀርብ ተመላክቷል።
አምስተኛው ደግሞ የክልሎች የቱሪዝም መስህቦችን ሲሆን÷ ክልሎች ያሏቸውን እና ይወክሉናል የሚሉትን የሚያሳዩበት ነው ተብሏል።
ይህም የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና እሴት ለዓለም ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው።
በፍቅርተ ከበደ