ከንቲባ አዳነች ከብሉምበርግ ፊላንትሮፒ የትራፊክ አደጋ ጉዳት ዘርፍ ኃላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከብሉምበርግ ፊላንትሮፒ የትራፊክ አደጋ ጉዳት ዘርፍ ኃላፊ ሚስ ኬሊ ላርስን እና አብረዋቸው ከሚሰሩት የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት እና የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በከተማችን የትራፊክ ማኔጂመንት እና ሴፍቲ ስትራቴጂካዊ እንዲሁም ኦፕሬሽናል ጉዳዮች ትብብር ዙሪያ በሰፊው ተወያይተናል ብለዋል።
ከተማችን እስካሁን በዘርፉ ላስመዘገበቻቸው ወጤቶች እና ተምሳሌትነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸውልናል ሲሉ ጠቅሰዋል።
ተቋማቱ እስካሁን ላደረጉት አጋርነት ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባዋ፤ ትብብራቸውን ለማስቀጠል እና ከተማችን በማሳየት ላይ ወደምትገኘው እድገት እና ሽግግር የሚመጥን ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተናል ሲሉ ገልጸዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!