Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በቀብሪደሀር ከተማ የአስፋልት መንገዶችን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በቆራሃይ ዞን ቀሪደሀር ከተማ የተከወናወኑ የአስፋልት መንገዶችን አስመርቀዋል፡፡

በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራር በከተማዋ የተገነቡ የ2 ነጥብ 53 ኪ.ሜ. አስፋልት መንገዶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ልዑኩ በከተማው የተሰሩ ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮችንም ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በከተማዋ የሚገነባ ልዩ የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል ግንባታ ለማስጀመር የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የሆስፒታሉ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

በመርሃግብሩ ላይ አቶ ሙስጠፌ እንደገለፁት፤ በወሊድ ምክንያት እናቶች ለመውለድ ወደ ሩቅ ይሄዱ የነበረውንና ካለው የህዝብ ብዛት በቀብሪደሃር ሆስፒታል ያለው ጫናን ይቀንሳል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.