Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ሳምንት ዓውደ ርዕይ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ሳምንት ዓውደ ርዕይ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዓውደ ርዕዩ “ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ታሪክ፣ አሁን የደረሰበትን እና የቀጣይ ስራን የሚያሳዩ ፕሮግራሞች ይታዩበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በዓለም ተቋማትና ድርጅቶች መመስረትና በመምራት ያላትን የገዘፈ የዲፕሎማሲ ታሪክም የማሳየት አላማ ያለው ዓውደ ርዕዩ፤ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ታሪክ በማሳየት በአፍሪካ ቀንድ፣ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የተጫወተችውን ሚና ይታይበታል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.