የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ አባላት የህዳሴ ግድብን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ አባላት ታላቁ የኢትየጵያ የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የሴቶች ሊግ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም መድረክ እንደቀጠለ ነው።
በዛሬው እለትም የሊጉ ስራ አስፈፃሚ አባላት በጉባ እየተገነባ የሚገኘውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መስከረም አበበ÷ ግድቡ ከፍፃሜው እስኪደርስ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤቱ በቀጣይ ሰፋፊ ስራዎችን ለመስራት እቅድ መያዙን ገልጸዋል።
በዚህም በሚካሄዱ ንቅናቄዎች ላይ ሴቶች እንደ አሻራቸውን እያሳረፉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሊጉ ለህዳሴ ግድብ ከክረምት ወራት ጀምሮ ከፍተኛ ንቅናቄ በማካሄድ ከ127 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ መፈፀሙ ተገልጿል።