Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ጽ/ቤትና ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ጽ/ ቤት እና ከአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሃይማኖት አባቶች ጋር የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን የሃይማኖት አባቶች ገልጸዋል፡፡

ቤተ-ክርስቲያኒቷን የማይወክሉ ንግግሮችን እና ድርጊቶችን ፈፅሞ እንደሚያወግዙ ይህንንም ለምዕመናቸው ግልፅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ፥ በዩኔስኮ በቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል አከባበር ሀገራዊ ቅርስ እንደመሆኑ በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የሃይማኖት አባቶቹ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::

የሃይማኖት አባቶቹ የከተማ አስተዳደሩ ለበዓሉ አከባበር የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል::

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.