Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል የ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት እና አጋሮቹ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል የ2 ነጥብ7 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአማራ፣ ትግራይ፣ አፋር እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እና አጎራባች የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘላቂ ድጋፍ ማድረግ የሚስችል ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት፣ ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት፣ ከጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ፣ ከዴንማርክ ቀይ መስቀል እና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ለመርሐ ግብሩ ትግበራ የተመረጡት አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ በግጭት የተጎዱ፣ ከፍተኛ ተፈናቃዮች ወይም ከስደት ተመላሾች ያሉባቸው እንደሆኑ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮግራሙ ለአካታችነትን ትኩረት በመስጠት ሴት እማዎራዎችን፣ አረጋውያንን፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችን እና አካል ጉዳተኞችን ግምባር ቀደም ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.