Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ’የመደመር ትውልድ’ መጽሐፍ ሽያጭ የሚገነባው ሙዚየም ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራ በሆነው ‘የመደመር ትውልድ’ መጽሐፍ ሽያጭ የሚገነባው “የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙዚዬም” የግንባታ ሥራ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

ግንባታው በ18 ወራት እንዲጠናቀቅ የጊዜ ገደብ መቀመጡን እና አሁን ላይም የመሠረት ቁፋሮ ሥራው መጀመሩን የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር የሕዝብ ግንኙነትና ፕሮቶኮል ዘርፍ ኃላፊ አድማሱ ተክሌ ተናግረዋል፡፡

በአሶሳ ከተማ ውስጥ ለሚገነባው ሙዚየም 247 ሚሊየን 274 ሺህ 688 ብር ወጪ እንደሚደረግበትም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ሙዚየሙ ከመሬት በላይ ባለ ሁለት ወለል ሆኖ እንደሚገነባ ጠቁመው÷ ሌሎች ባሕላዊ ጎጆዎችና ካፌ ራሳቸውን ችለው እንደሚገነቡም አመላክተዋል፡፡

በአጠቃላይ የግቢው ስፋትም 6 ሺህ 145 ካሬ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ ሕንጻውና ጎጆዎቹ 1 ሺህ 110 ነጥብ 8 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፉ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

ቀሪው የግቢው ክፍል መዝናኛ እና አረንጓዴ ሥፍራ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.