Fana: At a Speed of Life!

የወንጪ ዳንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በማልማት ሒደት ግዙፍ የመሰረተ ልማት ሥራ ተሰርቷል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጪ ዳንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በማልማት ሒደት ግዙፍ የመሰረተ ልማት ሥራ ተሰርቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ወንጪ ሁሌም ንፁህ የተፈጥሮ ስጦታ ሆና ቆይታለች ብለዋል፡፡

የተፈጥሮን ድንቅ በረከት ተቀብሎ ተንከባክቦ እና አበልፅጎ መጠቀም ደግሞ የኛ የሰውልጆች ተጠባቂ ተግባር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የወንጪ ዳንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በማልማት ሒደት በግንባታው ምዕራፍ ከ8 ሺህ እስከ 12 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አንስተዋል፡፡

ግዙፍ የመሰረተ ልማት ስራ ተሰርቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ ለዚህም 43 ኪሎ ሜትር መንገዶች፣ 35 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብራት እና የኃይል አቅርቦት እንዲሁም 72 ሜትር ድልድይ እና ትምህርት ቤት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

የአካባቢው ወጣቶች ታላላቅ የልማት ሥራዎች ይዘው የሚመጡትን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማጣጣም እንደጀመሩም ጠቅሰዋል፡፡

ሰፊው የአካባቢው ማኅበረሰብም አሁን የላቀ የተጠቃሚነት ዕድል አግኝቷል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጽሑፋቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.