የሽግግር ፍትኅ የፖሊሲ ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽግግር ፍትኅ የፖሊሲዝግጅትና በጉዳዩ ላይ በቀጣይ መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን የፍትኅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የፍትኅ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ በላይሁን ይርጋ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ የምሥራቅ አፍሪካ ጽኅፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቻርለስ ክውሞኢ የፖሊሲ ዝግጅቱን እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሽግግር ፍትኅ ፖሊሲውን የሚያስፈፅሙ ልዩ ተቋማት እንደሚቋቋሙ አቶ በላይሁን ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም የሕግ ማዕቀፎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ አጠቃላይ ሂደቱን ከማስተባበር አንፃር ፍትኅ ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን መሥራቱን እንደሚቀጥል ገልጸው፤ የሰብዓዊ መብት ቢሮው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ቻርለስ ክውሞኢ በበኩላቸዉ በሽግግር ፍትኅ ፖሊሲ ዝግጅት ላይ ቢሯቸዉ ድጋፍ ሲያደረግ መቆየቱን አስታውሰው÷ ፖሊሲውን ለማዘጋጀት በተቋቋመው ቡድን በኩል የተሠራውን ሥራ እና የቀረበውን ምክረ ሐሳብ አድንቀዋል።
በቀጣይም ቢሮዉ የፖሊሲ ዝግጅት ሂደቱን በመደገፍ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን መግለጻቸውን ከፍትኅ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ተቋማቱ የሪፎርም እና የዐቅም ግንባታ ሥራዎችን በተመለከተም ውይይት የተደረገ ሲሆን ትብብራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!