ከ15 ሚሊየን ሔክታር በላይ ማሣ ላይ የነበረ ሰብል ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ታኅሣስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በ15 ሚሊየን 24 ሺህ 836 ሔክታር ማሣ ላይ የሚገኝ ሰብል መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የመኸር ሰብል መሰብሰብ በተጀመረባቸው ክልሎች እስከ ታኅሣስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ብቻ በባሕላዊ መንገድ 13 ሚሊየን 830 ሺህ 786 ሔክታር ማሣ ሰብል መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ከበደ ላቀው ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም በኮምባይነር 1 ሚሊየን 194 ሺህ 50 ሔክታር ላይ የሚገኝ ሰብል መሰብሰቡንም ገልጸው፤ በአጠቃላይ 15 ሚሊየን 24 ሺህ 836 ሔክታር ላይ የነበረው ሰብል መሰብሰቡን ተናግረዋል።
ከዚህ ከ8 ሚሊየን 532 ሺህ 171 ሔክታር ሰብሉ ተወቅቶ 220 ሚሊየን 457 ሺህ 352 ኩንታል ምርት መገኘቱን አመልክተዋል።
በ2015/16 የመኸር ሰብል ልማት 17 ሚሊየን 390 ሺህ 818 ሔክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ በተከናወነ ሥራ 17 ሚሊየን 548 ሺህ 694 ሔክታር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን አስታውሰዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!