ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዩኒሴፍ ተወካይ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር አቡበከር ካምፖን ጋር መከሩ፡፡
በውይይቱ ድርጅቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየሰራ ስላለዉ ዘርፈ ብዙ በጎ ሥራዎች ላይ መክረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አጋር የሆነው ዩኒሴፍ የልጆችን ሕይወት ለማዳንና መብታቸውን ለመጠበቅ ለሚያደርገው አስተዋጽኦ ምስጋና በማቅረብ አበረታትዋል፡፡