ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚያቸውን ረቱ

By Feven Bishaw

January 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማን እንዲሁም ወላይታ ድቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸንፈዋል፡፡

9፡00 ሠዓት ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ ከመረብ ባገናኛት ብቸኛ ጎል ፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማን አሸንፏል፡፡

ዐፄዎቹ 1 ለ0 ማሸነፋቸውን ተከትሎም በ18 ነጥብ 5 ደረጃን ሲይዙ፤ ወልቂጤ ከተማ በ8 ነጥብ 14 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም 12፡00 ሠዓት ላይ በተካሄደ ሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ወላይታ ድቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0 ረትቷል፡፡

አዛሪያስ አቤልም ጎሏን አስቆጥሯል፡፡

በውጤቱ መሠረትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ23 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ አናት ላይ ሲቀመጥ÷ ድቻ በ17 ነጥብ 6 ደረጃን ይዟል፡፡