Fana: At a Speed of Life!

በአለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን ለ33ኛ ጊዜ ሲከበር በአገራችን ደግሞ ለ28ኛ ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ “ወጣቶችን ከኢንዱስትሪ ተፅዕኖ በመከላከል፣ ከትምባሆ እና ኒኮቲን ጠንቆች እንጠብቃቸው!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን ፤በኢትዮጵያ ደግሞ “የትምባሆ ምርቶችን ባለመጠቀም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጉዳት እንከላከል!” በሚል መሪ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የትምባሆ ኢንዱስትሪ ገቢውን ለማስቀጠል ወጣቱ ላይ እያነጣጠረ ነው ያለው አለም የጤና ድርጅት መረጃ ምርቶቹም በትምህርት ቤት አከባቢዎች እና ወጣቶች በብዛት በሚገኙባቸው ስፍራዎች ለሽያጭ ይቀርባሉ።

እንዲሁም ትምባሆ ሳንባን እና ሌሎች የአካል ክፍሎችን የሚጎዳ ሲሆን አጫሾች በኮቪድ 19 የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን መረጃው ያሳያል ፡፡

በአለም በየዓመቱ ከ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች በትምባሆ ምርቶች ምክንያት ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.