የማዕድን ዘርፉ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ጉልህ ሚና እንዲኖረው እየተሠራ ነው-ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ዘርፉ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ጉልህ ሚና እንዲኖረው መሰረት የሚጥሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የማዕድን ዘርፉ ዋነኛ ትኩረት የውጪ ምንዛሬ ማስገኘት፣ ከውጪ የሚገቡትን ምርቶች በሀገር ውስጥ መተካትና የሥራ ዕድል መፍጠር መሆኑን የማዕድን ሚኒስትሩ ሐብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ጠቅሰዋል፡፡
የወርቅ ምርትን ጨምሮ ሌሎች ማዕድናትን ወደ ውጪ በመላክ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት አመርቂ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በባህላዊ መንገድ ከሚመረተው ወርቅ በተጨማሪ በፋብሪካ ደረጃ በጥራትና በብዛት እንዲመረት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ለዚህም አምስት ያህል ፋብሪካዎች ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
እንደ ድንጋይ ከሰል እና ሲሚንቶ ያሉ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እየተመረቱ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!