የሀገር ውስጥ ዜና

በአለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን እየተከበረ ነው

By Feven Bishaw

May 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን ለ33ኛ ጊዜ ሲከበር በአገራችን ደግሞ ለ28ኛ ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ “ወጣቶችን ከኢንዱስትሪ ተፅዕኖ በመከላከል፣ ከትምባሆ እና ኒኮቲን ጠንቆች እንጠብቃቸው!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን ፤በኢትዮጵያ ደግሞ “የትምባሆ ምርቶችን ባለመጠቀም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጉዳት እንከላከል!” በሚል መሪ እየተከበረ ይገኛል፡፡