ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከአየርላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በግብርና ልማት ሥራዎች ላይ በኢትዮጵያ ከአየርላንድ አምባሳደር ኒኮላ ብሬናን ጋር ተወያዩ፡፡
በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የግብርና ሽግግር ለማምጣት ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን እየተሠራ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የግብርናውን ምርታማነት ለመጨመርና ለግብርና ሽግግር ትልቅ ድርሻ እንዳላቸውም አስረድተዋል፡፡
ሜካናይዜሽንና ሌሎች የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ግብርናውን ለማዘመን እየተሠራ መሆኑንና የሽግግሩ መንገድ መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የሚውል በርካታ የውኃ ሃብት ክምችት እንዳላትና የግብርናውን ዘርፍ ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በመስኖ ልማት ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ለዚህም በመስኖ ስንዴ ልማት የመጣው ለውጥ ትልቅ ማሳያ ነው ማለታቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ላይ ከማምረት ጀምሮ እስከ ማዕድ ድረስ ባለው ሰንሰለት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
አየርላንድም በዚህ ረገድ ያላትን ተሞክሮ በማካፈልና ድጋፍ በምታደርግበት ዙሪያ መክረዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት የረጂም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት ታሪክ ያላቸው እንደመሆናቸው በግብርናው መስክ ምርታማነትን ለማሳደግ እያደረጉት ያለውን ትብብር በማጠናከር በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩ ተመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!