Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ስምምነቱ ዘላቂ የልማት ትስስርን ያጠናክራል አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በሶማሊ ላንድ መካከል ሁሉን አቀፍ የትብብርና የአጋርነት መግባቢያ ስምምነት ሠነድ መፈረሙ መልካም ጉርብትናን በመፍጠር ዘላቂ የልማት ትስስርን እንደሚያጠናክር የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ በኢትዮጵያና ሶማሊ ላንድ ከሣምንት በፊት የተፈራረሙትን ስምምነት አስመልክቶ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ÷ ስምምነቱ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ከማድረጉም ባለፈ ያለንን መልካም ጉርብትና ያጠናክራል ብለዋል፡፡

በተለይም ክልሉ ካለው የእንስሳት ሃብት የተሻለ ጥቅም እንዲያገኝ የሚያስችል ስምምነት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የክልሉ አርብቶ አደር ለእንስሳቱ ገበያ የተሻለ አማራጭን ያስገኝለታል ማታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርኅ የወታደራዊ ቤዝና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት ለማግኘት የደረሰችው ስምምነት መልካም ጉርብትናን በማምጣት ሌላውን ሳንጎዳ የሀገራችንን ስብራት የሚጠግን ነውም ብለዋል፡፡

ስምምነቱ ጸጋዎችን በጋራ በማልማት አብሮ ለማደግ ያለውን የመንግስት ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.