Fana: At a Speed of Life!

3 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ማግኘታቸው ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስካሁን 3 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ ማግኘታቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

የፕሮግራሙ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ እንዳሉት÷ ዲጂታል መታወቂያ የአሠራር ክፍተቶችን በመቀነስ ከሙስናና ብልሹ አሠራር የጸዳ አገልግሎትን ለመስጠት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አሰራር ለማዘመንና ዲጂታል ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አንስተዋል፡፡

ዲጂታል መታወቂያ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዲጂታል ኢኮኖሚ እውን ለማድረግ እና ለሀገር እድገት ወሳኝ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ዲጂታል መታወቂያን በተለያዩ ተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን ጠቁመው÷ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁንም ከተቋማት በተጨማሪ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ማግኘታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በተለያዩ ማዕከላት እየተካሄደ ነው ያሉት አቶ አቤኔዘር÷ ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.