Fana: At a Speed of Life!

የወንጪ – ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር የብዙ እድሎች መግቢያ በር ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጪ – ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር የቱሪዝም ማዕከል ብቻ ሳይሆን የብዙ እድሎች መግቢያ በር ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ።
ርእሰ መስተዳድሩ ፕሮጀክቱ ገቢ በማመንጨት፣ የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም ስራ ፈጠራን በማበረታታት ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተናግረዋል።
መንደሩ ዘላቂ ቱሪዝምን ለማልማት፣ የተፈጥሮ ውበትና ባህላዊ ሀብትን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚረዳም ገልፀዋል።
መንደሩ ከተለያዩ የባህል ተሞክሮ የተውጣጡ ሰዎችን በማሰባሰብ ለመግባባት በር እንደሚከፍት ጠቅሰው፤ ጎብኚዎች የአካባቢውን ባህል፣ ወግና የአኗኗር ዘይቤዎች እንዲረዱ እድል ይሰጣል ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት ለዚህ የኢኮ ቱሪዝም መንደር እውን መሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቅረበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ፣ ገቢ በማሰባሰብና ጠንካራ ክትትል በማድረግ ፕሮጀክቱ በታሰበው ጥራትና በተያዘው ጊዜ እውን እንዲሆን በማስቻላቸው ርዕሰ መስተዳድሩ በራሳቸው እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.