Fana: At a Speed of Life!

 የፌዴራል ፖሊስ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ማኅበር እንዲጠናከር ድጋፍ ይደረጋል –  ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ማኅበር እንዲጠናከር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የቀድሞ ሠራዊት ድጋፍና ልማት ማኅበር ውይይት እያካሄደ ነው።

የማኅበሩ የበላይ ጠባቂ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚህ ወቅት እንደገለጹት ፥ ዘመናዊ የፖሊስ ሠራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የቀድሞ የሠራዊቱ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የፖሊስ ሠራዊት የቀድሞ አባላት የካበተ ልምድ እና ዕውቀት ያላቸው በመሆኑ በተቋምና በሠራዊት አቅም ግንባታ የላቀ አበርክቶ እንደሚኖራቸው አንስተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሀገራቸውን አገልግለው ጡረታ የወጡ አባላትን ማኅበሩ መሰብሰቡን ጠቅሰው ፥ አባላቱ ያላቸውን ልምድና አቅም አሁን ላሉት የሠራዊት አባላት በማጋራት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሀገሩን እና ሕዝቡን በስነ-ምግባር፣ በጀግንነት እና በሰብዓዊነት የሚያገለግል የፖሊስ ሠራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የጀመረው የሪፎርም ሥራ በተሻለ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ፥ ዘመናዊ የፖሊስ ሠራዊት ለመገንባት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በታሪኩ ወ/ሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.