1 ሺህ ጥንዶች የሚዳሩበት የሰርግ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ ሁለት ሺህ ሙሽሮች (አንድ ሺህ ጥንዶች) የሚዳሩበት የሰርግ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የመጡ ጥንዶች የተሳተፉበት የሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ በባህላዊ ዘፈኖችና በልዩ ልዩ ትዕይንቶች ታጅቦ ነው በሚሊኒየም አዳራሽ እና ፒኮክ አደባባይ የተካሄደው፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሺህ ጋብቻ የማኅበረሰብ ዋነኛ መሠረት የሆነውን ትዳር የሚያበረታታና የባህል እሴትን አጉልቶ የሚያሳይ መድረክ ነው ብለዋል፡፡
የሺህ ጋብቻ አያሌ ጥንዶች በአንድ የሚሞሸሩበት ከመሆኑ ባለፈ÷ በየአካባቢው ያሉ ባህሎች ጎልተው በመውጣት ለዓለም እንዲተዋወቁ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይ የጋብቻ ሂደትን አጠቃላይ በሚያሳይ ሥነ-ሥርዓት ጥንዶች የሚሞሸሩበትን ሥርዓት ለመፍጠር እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!