Fana: At a Speed of Life!

የሃላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ሴራ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሴራ” በዓል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በሃላባ ቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ ከፌዴራል ፣ ከክልሎችና ከዞን አስተዳደሮች የመጡ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዓሉ ለአንድ ወር በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ሲከበር የቆየ ሲሆን ÷ በዛሬው ዕለትም የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ በሃላባ ሁለገብ ስታዲየም በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በመከበር ላይ ነው ።

በብሔረሰቡ መንገሳ ተብሎ በሚጠራው የታሕሳስ ወር ላይ የሚከበርና ለወራት ከፍተኛ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሴራ በዓል ወቅት የተጋጩትን በማስታረቅ፣ በአብሮነትና በፍቅር የሚታለፍበት ድንቅ ባሕል በመሆኑ በየዓመቱ በናፍቆት ይጠበቃል ።

በበዓሉ ወቅት አባቶች የተጣሉትን በማስታረቅ በፍቅር በዓሉን እንዲያከብሩ ጥረት የሚያደርጉበት፣ ህፃናት ከልጅነት ወደ ወጣትነት የሚሻገሩበት እና ሃላፊነት የሚቀበሉበት ሥርዓት የሚፈፀምበት ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ዕድሜያቸው የደረሱ ልጃገረዶች ጎጆ የሚመሰርቱበትና ሌሎች በርካታ እሴቶችን በውስጡ የያዘ በዓል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

እሴቱን የዓለም ቅርስ ለማድረግ እንዲሁም በዩኔስኮ ለማስመዝገብም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሃላባ ዞን አስተዳደር አስታውቋል ።

በብርሃኑ በጋሻው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)e
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.