Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ተመዝብሮ የነበረ 90 ሚሊየን ብርና ከ40 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ እንዲመለስ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ተመዝብሮ የነበረ 90 ሚሊየን ብር እና ከ40 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ለመንግስት እንዲመለስ መደረጉን የክልሉ ሥነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ አዳል ሙላት እንዳሉት÷ ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎችን በመለየት የመንግስት እና የሕዝብ ሃብት እንዳይባክን በትኩረት ተሰርቷል፡፡

በተለይም በመሬት ነክ ጉዳዮች፣ በገቢና ታክስ፣ በፕሮጀክቶች እና ግዢ ዘርፎች ላይ የሙስና ድርጊት የመከላከል ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም ያለአግባብ ተመዝብሮ የነበረ 90 ሚሊየን ብርና ከ40 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የሆነ ቦታ እንዲመለስ መደረጉን ነው የገለጹት፡፡

ከሕገ-ወጥ ድርጊቱ ጋር በተያያዘ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች እና ተቋማት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየቱን ጠቁመዋል፡፡

የሙስና ወንጀልን መንግስት በሚያደርገው ጥረት ብቻ መከላከል አይቻልም ያሉት ኮሚሽነሩ÷ ሕበረተሰቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

በተለይም ለሀገሩ በታማኝነት እና በቅንነት የሚሰራ ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡

በመላኩ ገድፍ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.