Fana: At a Speed of Life!

የአደባባይ በዓላት በሠላም እንዲከናወኑ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወኑ በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ገለጹ፡፡

ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የሚሠሩ ከ11 ሺህ በላይ ተጨማሪ የሰላም ሠራዊት አባላት ሰልጥነው ወደ ሥራ መግባታቸውን ኃላፊዋ አስታውቀዋል፡፡

የሰላም ሠራዊት አባላቱ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ  መሆናቸውን እና ከዛሬ ጀምሮም የመዲናዋን ሰላም የማስጠበቅ ሥራ ያከናውናሉ ማለታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

የመዲናዋን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ መልኩ የማስጠበቅ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ያመላከቱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.