በኦሮሚያ ክልል ከ22 ሚሊየን በላይ የአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት መማሪያ መጽሐፍ ተሰራጨ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል እስካሁን ከ22 ሚሊየን በላይ የአዲሱ ሥርዓተ-ትምህረት መማሪያ መጽሐፍ መሰራጨቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ትምህር ቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን እድሪስ÷ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም የአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት መማሪያ መጽሐፍ ለተማሪዎች በወቅቱ እንዲደርስ በትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሕትመት ሒደቱን ለማፋጠንም በመንግስት አስፈላጊው በጀት ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡
እስካሁንም 15 ነጥብ 5 ሚሊየን የአንደኛ ደረጃ እና 6 ነጥብ 6 ሚሊየን የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍ መሰራጨቱን አስገንዝበዋል፡፡
ቢሮው ቀሪ የመማሪያ መጽሐፍትን በፍጥነት አሳትሞ ለተማሪዎቸ ተደራሽ እንደሚያደርግም አቶ ሃሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ